Tesfa Birhan secondary School
Home የ12ኛ ክፍል ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

የ12ኛ ክፍል ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

20th April, 2025

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ ፥ " ይሄ አራተኛው ነው በአዲሱ የፈተና አሰጣጥ ፈተና የሚሰጥበት " ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከትምህርት ቤቶች ወጥቶ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አስገብቶ ፈተና እንዲሰጥ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ስለዘንድሮው የ2017 ዓ/ም ፈተና በተናገሩበት ወቅት 150 ሺህ ተማሪዎች ፈተናቸውን በኦንላይ እንዲወስዱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ብርሃኑ (ፕሮፌሰር) ፥ " እንደ ከዚህ ቀደሙ አድካሚ በሆነ ከቦታ ቦታ ልጆችን እያዘዋወሩ ከመሄድ ባለፈው ዓመት 29 ሺህ ተማሪ ነበር ኦንላይን ፈተና የሰጠነው ዘንድሮ ደግሞ 150 ሺህ ተማሪ ኦንላይን ፈተና ለመስጠት እየተዘጋጀን ነው " ብለዋል።

ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ቆርጠው ባይናገሩም ፈተናው ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንዲሰጥ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

Via : ቲክቫህ ኢትዮጵያ

.

Copyright © All rights reserved.

Created with